ስለ ቀቤና
የቀቤና ብሔረሰብ በጉራጌ ዞን ከሚገኙ ብሔረሰቦች መካከል አንዱ ሲሆን በዋነኛነት በወልቂጤ ከተማና በቀቤና ወረዳ በሚገኙ 23 ቀበሌያት ሠፍሮ ይገኛል፡፡ ብዛት ያላቸውየብሔረሰቡ አባላት ከብሔረሰቡ ዋነኛ መገኛ ውጪ በተለያዩ ቦታዎች ማለትም በክልሉ ውስጥ በሲዳማ ዞን በበንሣ ወረዳ ፣ በጉራጌ ዞን በአበሸጌ ፣ በምሁር አክሊል ፣ በእነሞር እና ኤነር እና ማረቆ ወረዳዎች እንዲሁም በአላባ ልዩ ወረዳ ፣ በከምባታ ጠንባሮ እና በሀዲያ ዞኖች ከሌሎች ሕዝቦች ጋር በስብጥር እንደሚኖሩ የተለያዩ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ብሔረሰቡ የሚገኝበትን አካባቢ በሰሜን የኦሮሚያ ክልል የጐሮ ወረዳ፣ በደቡብ የእዣ እና የቸሀ ወረዳዎች በምዕራብ የአበሸጌ ወረዳ እንዲሁም በምስራቅ የኮኪር እና ምሁር አክሊል ወረዳዎች ያዋስኑታል፡፡
About Kebena Nation
Kebena is a distinguished nation having its own identity expressed by language of Cushitic family, dressing style, feeding habit, way of life, culture, cooperation and dispute resolution mechanisms which are in bodies in their traditionally law known as “Bobani Geltita” and enforced by their traditional elder assembly/council called “Oget” the principle of kebena traditional by-law believed to be adopted from Islamic law. Kebena people have its own separate woreda administration with 23 rural kebeles and wolkite town as administrative center, which is 155 km from Addis Ababa, which is national capital city of Ethiopia and 450 km from Hawasa, which is regional capital city of South Nation, Nationality and People (SNNP).
Historical places
There are century old mosques of “Katbare” and “Zebimola”, which have a great place in Islamic religion followers are found in kebena woreda. Others like underground caves, waterfalls and Hassan Enjamo versus Menelik-II war battle field called “Jebdu Meda” are also potential tourist attractions in the woreda. If these tourist attraction heritages protected and promoted, would be serve as assets for the society of kebena.
Culture Center
The people of Kebena have a significant part in the history of Ethiopia both in terms of religious and cultural values. They were pioneers in expanding Islamic Doctrine in the Sothern region of the country with strong leadership of Hassen Enjamo during the regime of Minillik II. This long history of the people can serve both as source of original research for those in related discipline and contribute to tourism development in nationwide context.
ሰለቀቤና ቋንቋ
የቀቤና ብሔረሰብ የአፍ መፍቻ ቋንቋ "ቀቤንኛ" ሲሆን ከኩሽ የቋንቋ ቤተሰብ ይመደባል፡፡ ቋንቋው ከሀላቢሳ፣ ከከምባትሣ፣ ከጠንባርሳ እና ከሲዳምኛ ቋንቋዎች ጋር እንደሚቀራረብና አብዛኛው የብሔረሰቡ አባላት ፣ ከነዚህ ቋንቋ ተናጋሪ ሕዝቦች ጋር ያለ አስተርጓሚ መግባባት እንደሚችሉ ከአካባቢው የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በአጐራባች አካባቢዎች የሚገኙ የብሔረሰቡ አባላት ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በተጨማሪ ጉራግኛንና ኦሮምኛን በሁለተኛ ደረጃ ይናገራሉ፡፡ ቀቤንኛ በአሁኑ ወቅት ከንግግር ቋንቋነት አልፎ የሥራ እና የትምህርት ቋንቋ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል፡፡ ለቋንቋው የጽህፈት አገልግሎት የሣባ ፊደል የተቀረፀለት ሲሆን በዚህም የቀቤንኛ-- አማርኛ መዝገበ ቃላት እና አንደኛ ደረጃ የመጀሪያ ሣይክል መማሪያና ማስተማሪያ መጽሐፍት በክልሉ ትምህርት ቢሮ አማካይነት ተዘጋጅተው አገልግሎት ላይ ውለዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ቋንቋው በአንደኛ ደረጃ ሁለተኛ ሣይክል ትምህርት ቤቶች እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡
We have 430 guests and no members online