ዘቢሞላ              

ዘቢሞላ በደቡብ ክልል በቀቤና ወረዳ ከሚገኙ ታሪካዊ ቦታዎች(መስጂዶች) አንዱ ሲሆን የቀቤና ወረዳ ዋና ከተማ ከሆነችው ወልቂጤ 3 ኪሎ ሜትር በስተ ምስራቅ አቅጣጫ የሚገኝ ውብ የሃይማኖትና የታሪክ ማእከል ነው:: የዘቢሞላ ሃድራ የተቋቋመው በ18ኛው ክፍለ ዘመን ሲሆን ያቋቋሙትም የቀቤናው ታዋቂ አሊም ሐጂ ስሩር ሼህ በሺር (ኦቢዩ) ናቸው::

         

ኦቢዩ ዘቢሞላ ላይ የሰፈሩት የተለያዩ ቦታዎች ላይ ሐድራቸውን ለመመስረት ሙከራዎችን ካደረጉ በኋላ ነው፡፡ ዘቢሞላ ላይ ሐድራቸውን ለማቋቋም ካደረጋቸው ምክንያቶች አንዱ በመካ ላይ ያገኙት ሼህ ጥቆማ ነው፡፡ በወቅቱ ኦቢዩ ለዚህ ሼህ ያማከሩት ዋነኛ ነገር ቢኖር ቀልቤ ላይ ያለውን በሽታ የሚያድነኝ የሩሔ ሼህ ፈልጌ አላገኘሁም የሚል ነው፡፡ ሼሁም የሚዘከሩ አውራዶችን ለኦቢዩ ከሰጣቸው በኋላ ሀገራቸው ላይ በመሄድ የሸሪዐ ትምህርት እንዲያስፋፉ እና የሚሰፍሩበትም አካባቢ ምን አይነት ምልክት እነዳለው ገልጾላቸው ነበር፡፡ በመሆኑም ኦቢዩ ከዘቢሞላ በፊት በጣጤሳ እና ሩሙጋ ላይ የሰፈሩ ቢሆንም በሼሁ የተሰጣቸው ምልክት ፈጽሞ ተመሳሳይነት ስላልነበረው በመጨረሻም ዘቢሞላ ላይ ሰፈሩ፡፡

   

ኦቢዩ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ዘቢሞላ ሲመጡ ሶስት ወጣቶችን የእርሻ ስራ እየሰሩ አገኙ፡፡ እና ስማቸውን ጠየቋቸው፡፡ ወጣቶቹም ስማቸውን ተራ በተራ ተናገሩ፡- አንደኛው ዐብደላ ሲሆን ሁለተኛው ዐብዱ እና ሶስተኛው ሙኽታር ነበሩ፡፡ ኦቢዩም በተራቸው ስማቸው ሐጂ ስሩር መሆናቸውን ሲነግሯቸው ወጣቶቹ በቀላሉ አወቋቸው፡፡ ምክንያቱም በወቅቱ ኦቢዩ በቀቤና ማህበረሰብ ውስጥ በደንብ ይታወቁ ስለነበር ነው፡፡ በመቀጠልም ኦቢዩ እስልምናን በአካባቢው ለማስፋፋት እነደሚፈልጉ በመግለጽ ወጣቶቹ ለዚሁ የሚውል መሬት ከይዞታቸው ቆርጠው ለመስጠት ፍቃደኝነታቸውን ጠየቋቸው፡፡ ወጣቶቹም መሬታቸውን ለመስጠት ፍቃደኛ በመሆናቸው የዘቢሞላ ሐድራን ኦቢዩ ከእነኚህ ወጣቶች በተበረከተላቸው ቦታ ላይ መሰረቱ፡፡  

      

ስለ ኦቢዩ ተጨማሪ ለማንበብ ዳወንሎድ ያድርጉ

 

ስለ ዘቢሞላ ቅርሶች አያያዝ ቪዲዮ ይመልከቱ

 

 

 

 

 

 

We have 224 guests and no members online