ባህላዊ  አስተዳደር

የቀቤና ብሔረሰብወማበሚል የማዕረግ ስም በሚታወቁ ባህላዊ መሪዎች ይተዳደራል፡፡ወማዎች ለሥልጣን የሚበቁት በህዝብ ምርጫና ይሁንታ ብቻ ነው፡፡ በብሔረሰቡ 37 ጐሣዎች የሚገኙ ሲሆን በባህላዊ አስተዳደር ውስጥ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን የማየት ሥልጣን ያላቸው ሁሉም ጐሣዎች በሚወከሉበት ምልዐተ-ጉባኤ የሚመረጡ 12 ዳኞች ናቸው፡፡ ዳኞችም በህዝቡ መካከል የሚነሱ ግጭቶችን የሚፈቱት የእስልምና ኃይማኖትንና የብሔረሰቡን ባህላዊ የአስተዳዳር ህግን መሠረት በማድረግ ይሆናል፡፡ ይህ ባህላዊ ህግቦበኔ ኦዳወይምቦበኔበመባል ይታወቃል፡፡ ምንም እንኳን የብሔረሰቡ እስላማዊ መንግሥት መቼ አና እንዴት እንደተመሠረተ የሚገልፅ ተጨባጭ ማስረጃ ባይገኝም ቦበኔ መሠረቱቅዱስቁርአን እንደሆነ ይታመናል፡፡ቦበኔበብሔረሰቡ መካከል የሚከሰቱ  የነፍስ ማጥፋት ወንጀሎችን በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፍላቸዋል፡፡ እነሱም፡- “ሙሉ ደምመዳላእናየመዳላ መዳላበመባል ይታወቃሉ፡፡ በሁለቱ ደመኛ ወገኖች መካከል ታስቦና ታቅዶ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ የሚፈፀም ከባድ የግድያ ወንጀልሙሉ ደምይባላል፡፡ በድንገተኛ አጋጣሚ በሁለቱ ወገኖች መካከል በተፈጠረ ዕለታዊ ግጭት ምክንያት የሚፈፀም የግድያ ወንጀልመዳላሲባል የመጨረሻውና ዝቅተኛ ደረጃ የተሰጠው የግድያ ወንጀል ደግሞየመዳላ መዳላይባላል፡፡ ይህም በሁለቱ ወገኖች መካከል ምንም ዓይነት ዕለታዊ ግጭትም ሆነ ቂም ሣይኖር ባልታሰበ አጋጣሚ የሚፈፀሙትንና የነፍስ ማጥፋት ወንጀሎችን ያጠቃልላል፡፡

        

በማናቸውም መልኩ በብሔረሰቡ የነፍስ ማጥፋት ወንጀል ቢፈፀም ጉዳዩን የሚዳኙት ከሁለቱ /ከገዳይም ሆነ ከሟች/ ወገኖች ጋር ዝምድና ወይም የደም ትስስር የሌላቸው ገለልተኛ የአገር ሽማግሌዎች ናቸው፡፡ በአጥፊው ወገን ላይ የቅጣት ውሣኔ የሚሰጠውም ባህላዊውን ህግ /“ቦበኔ”/ መሠረት በማድረግ ይሆናል፡፡ ግጭቶቹም ወደከፋ ግጭት እንዳያመሩ ለመከላከልና ብሎም ከምንጩ ለማድረቅ ያገር ሽማግሌዎች ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋሉ; ወዲያው ድርጊቱ እንደተፈፀመ ወደ ሟች ወገኖች በመሄድየሞተውን ሰው ነፍስ አላህ ለጀነት ያድርገው! ለናንተም አላህ ፅናቱን ይስጣችሁ! ደም ስጡን!“ ጉዳዩን በሽምግልና ይዘን እንድናየው ፍቀዱልንበማለት ይማፀኗቸዋል፡፡ የሽማግሌዎቹ ልመና ከሟች ወገኖች እሺታን እስካላገኘ ድረስ የሟች አስከሬን አይቀበርም; ከአዎንታዊ ምላሽ በኋላ ግን አስከሬኑ ይቀበራል፡፡ የገዳይ ወገኖችም ጉዳዩን በያዙት ሽማግሌዎች እጅ ብር 2ዐዐዐ ያስይዛሉ፡፡ ሽማግሌዎቹም ደከመን ሰለቸን ሳይሉ የፀቡን መንስኤ በጥልቀት ማጥናት ይጀምራሉ፡፡ ይህ በሽማግሌዎች የተጀመረው ወንጀልን የማጣራት ተግባር እስከሚጠናቀቅ ድረስ ገዳይና  የቅርብ ዘመዶቹ ቀድመው የሚኖሩበትን ቀዬ ለቀው እንዲሄዱ;የሟች ወገኖች በሚዘዋወሩበት አካባቢ እንዳይዘዋወሩ በሚገበያዩበት አንዳይገበያዩ በሽማግሌዎች አማካኝነት ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ይሰጣቸዋል፡፡ የሟች ወገኖችም ቢሆኑ ወደ መደበኛው ፍርድ ቤት ሄደው ክስ እንዳይመሠርቱ ይታዘዛሉ፡፡ ይህ ትዕዛዝምከተራይባላል፡፡ ይህን የሽማግሌዎችን ትዕዛዝ ተላልፎ የተገኘ ወገን ቦበኔሥርዓትና ህግ መሠረት ይቀጣል፡፡

ቀዬአቸውን ጥለው አንዲሄዱ የተደረጉት ገዳይና የገዳይ የቅርብ ዘመዶች ወደ ትዉልድ ቀዬአቸው እንዲመለሱ የሚፈቀድላቸውየጉዳገዳይ በሽማግሌዎች ፊት ቀርቦ የእምነት ክህደት ቃሉን የሚሰጥበት የብሔረሰቡ ባህላዊ የወንጀል ምርመራ ሥርዓት ከተፈፀመ በኋላ ነው፡፡ በዚህ ጉዳሥርዓት ላይ ገዳይ ቢዋሽ ወይም የተሳሳተ መረጃ ቢሰጥበእርሱና በዘር ማንዘሩ ላይ መቅሰፍት ይወርዳልተብሎ ስለሚታመን ፈፅሞ አይዋሽም; ድርጊቱን ከነአፈፃፀሙ አንድ ሳያስቀር ይናዘዛል፡፡ ሽማግሌዎችም ሁሉንም አጣርተው ከመረመሩ በኋላ ለወንጀሉ አፈፃፀም ደረጃ ይሰጡታል፡፡ እንደ ወንጀሉ ዓይነትም ቦበኔ ህግ መሠረት በማድረግ ቅጣት ይወስናሉ፡፡ የተፈፀመወ ወንጀል ከፍተኛ ወይምየሙሉደምከሆነ ከብር 15 ሺህ እስከ 2 ሺህ ድረስ ገዳዩ ካሣ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡ ወንጀሉ መደላወንጀል ከሆነ ደግሞ የመጀመሪያውን ግማሽ ብርመደላ መደላከሆነም አንዲሁ የመጀመሪያውን ሲሶ ካሣ እንዲከፍል እንደሚደረግ እና ሁለቱም ወገኖች ደግመው ለፀብ እንዳይፈላለጉ ማሠሪያ ተበጅቶ የእርቁ ሥነ ሥርዓት እንደሚጠናቀቅ የአካባቢው አዛውንቶች ይናገራሉ፡፡ በቀቤና ብሔረሰብ ሴቶች ከፍተኛ ማህበራዊ ቦታ አንዳላቸው ይነገራል፡፡ አብዛኛው የብሔረሰቡ አባላት የእስልምና ኃይማኖት ተከታይ በመሆናቸው ሴቶች በኃይማኖት ሥነ-ምግባር ታንፀውና ተኮትኩተው እንዲያድጉ ይደረጋል፡፡

የጋብቻ ሥርዓት

የጋብቻ  የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወጣቶች ለጋብቻ ብቁ መሆናቸው የሚገልፁባቸው የተለያዩ መንገዶች አሉዋቸው፡፡ ለምሣሌ አንዲት ልጃገረድ ለአቅመ ሔዋን መድረሷን ለማመልከትናኦታወይምጨረርየተሰኘውን ባህላዊ የፀጉር አሰራር ትሠራለች፡፡ የግል ቤትና ንብረት እንዲኖረው መፈለግና ይህም እንዲሟላለት ለወላጆቹ ጥያቄ ማቅረብ ደግሞ ወንዱ ለአቅመ አዳም መድረሱን የሚገለፅበት መንገድ ነው፡፡

በቀቤና ብሔረሰብ ሰባት የጋብቻ ዓይነቶች አሉ; እነሱም፡- “አጩቁ”- የሚባለውና በወላጆች መልካም ፈቃድ የሚፈፀም ጋብቻ፣ጌሡ”- በጠለፋ ወይም በኃይል የሚፈፀም ጋብቻ፣ጣጦቄን አዩ”- ድንገቴ የጋብቻ ዓይነት ሲሆን ጋብቻ፣ረጋኡ” - የውርስ ጋብቻ፣ዶርቱታ”- የምትክ ጋብቻ፣ወጌቲታ”- የፈት ጋብቻ፣ሙሪታ ባዬን አሱ”- የሴቷ ወላጆች ለልጆቻቸው የመረጡላትን ወንድ ጠርተው የሚድሩለት ጋብቻናቸው፡፡

ይሁን እንጂ በብሔረሰቡ ዘንድ በይበልጥ የሚዘወተሩት  “አጩቁአናጣጦቄን አዩንየተሰኙት የጋብቻ ዓይነቶች ብቻ ናቸው፡፡ አጩቁጋብቻ በወላጆች መልካም ፍቃድ የሚፈፀም የጋብቻ ዓይነት ሲሆን በዚህ የጋብቻ ሂደት ውስጥ ከፍተኛውን ሚና የሚጫወተው የወንዱ ወላጅ አባት አንደሆነ ይነገራል፡፡ አባት ለልጁ የወደፊት ሚስት ትሆንለት ዘንድ ወደመረጣት ልጃገረድ ቤተሰብ አብረውት የሚሄዱትን ሽማግሌዎችን የሚመርጠው እሱ ነው፡፡ ከመረጣቸው ሽማግሌዎች ጋር በመሆን ከልጅቷ ወላጅ አባት ቤት እንደደረሱምልጅህን ለልጄ ስጠኝየሚል የጋብቻ ጥያቄ የልጁ አባት ያቀርባል፡፡ በብሔረሰቡ የቆየ ልማድ መሠረት ለዚህ ዓይነቱ የጋብቻ ጥያቄአልሰጥም!” የሚል ቀጥተኛ ምላሽ ወዲያው መስጠትም ሆነ በማናቸውም መንገድ ጥያቄውን ይዘው የመጡትን ሽማግሌዎች አሳፍሮ መመለስ እንደፀያፍ ተግባር ይቆጠራል፡፡ ይህም ማለት ግን ለጥያቄው ሁሌም አዎንታዊ ምላሽ ይሰጣል; የጠየቀ ሁሉ ያገባል ማለት አይደለም፡፡ በቀጥታ አይሁን እንጂ ለሽማግሌዎች አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ምላሽ በተዘዋዋሪ የሚሰጥባቸውና በብሔረሰቡ የተለመዱ በርካታ መንገዶች አሉ; አጭር ወይም ረዥም ቀጠሮ መስጠት ዋነኛው ስልት ነው፡፡ የልጅቷ አባት በጉዳዩ ላይ ተማክሮ መልስ ለመስጠት ለሽማግሌዎቹ አጭር /ከሁለት ሣምንት ያልበለጠ/ ቀጠሮ ከሰጠ ጋብቻውን የፈቀደ ወይም በጋብቻው የተስማማ መሆኑን፣ ረዥም እስከ ሦስት ወር የሚቆይ ቀጠሮ ከሰጠ ደግሞ ጋብቻውን ያልፈቀደ  መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከሁለት ሣምንት ያልበለጠ ቀጠሮ የሚሰጣቸው ሽማግሌዎችም በቀጣዩ ቀጠሮ ሌሎች ሽማግሌዎችን ጨምረው ጫትና  ስኳር ይዘው  ወደ ልጅቷ ወላጅ አባት ቤት ይመለሳሉ፡፡  እንደተጠበቀውም  ከልጅቷ ወላጆች ልጃችንን አላህ ከሰጣችሁ እኛም ለልጃችሁ ሰጥተናልበማለት መስማማታቸውን ይገልፃሉ፡፡ ይህ የይሁንታ ምላሽ አንደተሰማም ኮርማ በሬ ታርዶ ይበላል፣  ኒካ” /ቀለበት/ ሥርዓትም ይፈፀማል፡፡ አንዲት የቀቤና ልጃገረድኒካከታሠረላት በኋላ ሌላ ማንም ወንድ አይደፍራትም፣ ትከበራለች፣ ትታፈራለችም፡፡ በሆነ አጋጣሚ በሌላ ወንድ ብትጠለፍ ወይም ብትደፈር ጠላፊው በቦኔህግ መሠረት ይቀጣል፡፡ ለድርጊቱምአቂድ” /ካሣ/ በብሔረሰቡ መንፈሳዊ መሪዎች አማካይነት ሁለቱም ወገኖች በቃላቸው ለመፅናትሰጥቻለሁ” “ተቀብያለሁበማለት ቃል ኪዳን  የሚገቡበት የቃል ኪዳን ሥርዓት ነው፡፡ ጠላፊው ወይም ደፋሪው ካሳ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡ የካሣው መጠንም በአማካይ 15ዐዐ-2ዐዐዐ ብር እንደሚደርስ ይገመታል፡፡

 

ሌላው በብሔረሰቡ የሚዘወተረው የጋብቻ ዓይነትጣጦቄን አዩየሚሰኘው የድንገቴ ጋብቻ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ጋብቻ አንዳንዴተጠምጥሞ ገባበሚል ስያሜውም ይታወቃል፡፡ አግቢው ወጣት ከጓደኞቹ ጋር በመሆን ሣይታሰብ በድንገት ከወደዳት ልጅ ወላጆች ቤት ገብቶአልወጣምበማለቱ ምክንያት የሚፈፀም ጋብቻ በመሆኑ ነውተጠምጥሞ ገባመባሉ፡፡ ይህ ዓይነቱ ጋብቻ ለልጅቱ ወላጆች ዱብዕዳ /ድንገተኛ/ ይሁን አንጂ ለተጋቢዎች ግን ድንገተኛ አይደለም፡፡ በሁለቱ ተጋቢዎች መካከል ቀደም ሲል በሚስጢር የተስማሙበት ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ ዓይነት ከነጓደኞቹ የገባው ወጣት ከየት አንደመጣ? ምን እንደሚፈልግ? ቤታቸውንም ለቆ እንዲወጣ በልጅቷ ወላጆች ቢጠየቅም አይወጣም; ቤታቸውን የሙጥኝ ይላል፡፡ ከልጅቱ ወላጆች የይሁንታን ምላሽ እስከሚያገኝ ድረስ ከገባበት ቤት ንቅንቅ አይልም፡፡ ልጅቷም ፍቅረኛዋተጠምጥሞ መግባቱንስታውቅ ወዲያው በቅርብ ጓደኞቹ ትታጀባለች፣ አፍታም ሣይቆዩ የልጁ ወላጆች ልጃቸው ካለበት ከልጅቷ ወላጆች ቤት ሽማግሌ ይልካሉ፡፡ በዚህ መልኩ ጉዳዩ በሽምግልና ያልቅና ልጅቷ ትሞሸራለች፡፡ በተሞሸረች በአንድ ሁለት ቀን ውስጥም ጋብቻው ይፈፀማል፡፡ የጥሎሽ ሥርዓትም በዚሁ ዕለት ይከናወናል፡፡ የሚሰጠው የጥሎሽ ዓይነትና መጠን እንደሰጪው የመስጠት አቅም ይወሰናል፡፡ ከብት፣ ብር እና የተለያዩ አልባሳት ይሰጣሉ፡፡ ሆኖም ግን ይህ የጥሎሽ መጠን መናር በርካታ ወጣቶች ከጋብቻ እንዲርቁና እንዲሸሹ  በማድረጉ ምክንያት የጥሎሹ መጠን ወደ 15 ብር ዝቅ አንዲል በባህላዊ የአስተዳደር ጉባኤ ተወስኗል፡፡

ነፍሰ-ጡር የሆነች የቀቤና ሴት ልትወልድ አንድ ወይም ሁለት ወር ሲቀራት አይብ እንዲሁም ክትፎ /ከጐመንና ከስጋ/ አዘጋጅታ ጐረቤቶቿንና የቅርብ ዘመዶቿን ትጋብዛቸዋለች፡፡ ተጋባዦችም በአፀፋው በሠላም አንድትገላገል ይፀልዩላታል፡፡ ይህ ዓይነቱ ሥርዓትምጀበፍቲሡይባላል፡፡ እንዲሁም  አሁን ቀረ እንጂ ጥንት አንዲት አራስ ሴት ከአራስ ቤት እስከምትወጣ ድረስ ወላጅ እናቷ ክትፎ አዘጋጅታ ከቤቷ ድረስ የምታመጣላትመገንቤሱታየሚባል ባህላዊ ሥርዓት ሁሉ እንደነበረ የአካባቢው አዛውንቶች ያስታውሳሉ፡፡      

    ባህላዊ የቤት አሠራር

ብሔረሰቡ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተለያየ መጠን ያላቸውን የሣር ቤቶች ይሠራል፡፡ ትልቅ የሣር ቤት ለቤተሰቡ መኖሪያነት ትናንሽ /“ሐለዋ”/ የሚባሉ የጐጆ ቤቶችን ደግሞ ለእንግዳ መቀበያነት ያዘጋጃል፡፡ በአንድ አካባቢ አንድ ትልቅ መስጊድ በጋራ አማካይ በሆነ ሥፍራ ላይ ሠርተው በጋራ እንደሚጠቀሙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ እንዲሁም ብሔረሰቡ የተለያዩ የእርሻ መሣሪያዎችንና የቤት መገልገያ ቁሣቁሶችን ራሱ አዘጋጅቶ ይገለገልባቸዋል፡፡ ከጠንካራ እንጨት፣ ጫፉ ሹል ተደርጐ የሚዘጋጀውናዜጌዛበመባል የሚታወቀው የእርሻ መሣሪያ ለዚህ ተጠቃሽ ነው፡፡በርኩማ” /የሴቶች መደገፊያ/ዳለጌ” /መቀመጫ/ ኮቤ” /ነጠላ ጫማ/ ብሔረሰቡ ከእንጨት የሚያዘጋጃቸው የመገልገያ መሣሪያዎች ናቸው፡፡ ከቆዳ -ለወንዶች ትራስ፣ ከቀንድ- የክትፎ መብያ ማንኪያ፣ ከሸክላዋዲያት” /ትልቅ የክትፎ ማዘጋጃ/ ከብሔረሰቡ የዕደ ጥበብ ውጤቶች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

         

ባህላዊ በዓላትን በተመለከተ በቀቤና ብሔረሰብ ከተለመዱት መንፈሳዊ በዓላት ውጭ ይህ ነው የሚባል ባህላዊ በዓል የለውም፡፡ የሚያከብራቸው በዓላትም በእስልምና ኃይማኖት ዘንድ የታወቁትን በዓላት ብቻ ነው፡፡የቀሳሌየብሔረሰቡ ባህላዊ ጨዋታ ነው፡፡ ቀጭንና ልምጭ እንጨት በመወርወር ይከወናል፡፡ ትግል የከፍታ ዝላይ፣ የፈረስ ግልቢያ /“ገሌተ አለዳ”/ ሩጫ ሌሎች የብሔረሰቡ ባህላዊ ጨዋታዎች ናቸው፡፡

ባህላዊ የአመጋገብ ሥርዓት

ገንፎ፣ የቡላ እንኩሮ እና የቆጮ ድፎ በሥጋ  በቀቤና ብሔረሰብ ዘንድ ከሚዘወተሩት ባህላዊ ምግቦች ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ጥንትሠርጉ ፊታየሚባልና ከገብስ የሚዘጋጅ ባህላዊ መጠጥም ብሔረሰቡ ያዘጋጅ እንደነበር ከጉራጌ ዞን ማስታወቂያና ባህል መምሪያ የተገኙ ምንጮች ያመለክታሉ፡፡

ባህላዊ የአለባበስ  ሥርዓት

ከጥጥ የሚዘጋጅ የሽመና ውጤቶችን መልበስ በቀቤናዎች ዘንድ የተለመደ ባህላዊ አለባበስ እንደሆነ የዕድሜ ባለፀጋዎች ይናገራሉ፡፡ አዛውንቶች ከጥጥ የተሠራ ነጭ ሱሪና ሸሚዝ ወገባቸው ላይ ይለብሳሉ፡፡ ሴቶች ከታች ቡልኮ በመቀነት ታጥቀው ከላይ ጥብቆ ይለብሳሉ፡፡ ፀጉራቸውን በነጭ ሻሽ እጃቸውን በአንባር ያስጌጣሉ፡፡ እንዲሁም ወጣቶች ደግሞ ከታች ሰፊ ቁምጣ ከላይ ደግሞ ጥብቆ መልበስ ያዘወትራሉ፡፡

የለቅሶ ሥርዓት

የብሔረሰቡ የሀዘንና የለቅሶ ሥርዓት ከእስልምና ኃይማኖት ሥርዓተ-ህግ /ከሼሪያ ህግ/ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በመሆኑም አንድ ሰው ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ የተጋነነ ለቅሶም ሆነ ሀዘን እምብዛም አይስተዋልም፡፡ የኃይማኖት /የስግደት/ ሥርዓት ይከናወናል፡፡ ከዚያምላኢላህ-ላኢላላህ…” እየተባለ አስከሬኑ ወደ ቀብሩ ቦታ ከተወሰደ በኋላ ግብአተ-መሬቱ ይፈፀማል፡፡

Bobani Geltita (Elders Asembly)

Kebena nation have  its own identity, dressing style, feeding habit, way of life, help culture, cooperation and dispute resolution mechanisms which are in bodies in their traditionally law known as “Bobani Geltita” and enforced by their traditional elder assembly/council called “Oget” the principle of Qebena traditional by-law believed to be adopted from Islamic law.

       

Kebena Elders Assembly(Oget)                  and                                Kebena Cultural Dress

The people of Kebena have its own Language called “Kebensina”, It is part of the Lowland East Cushitic group within the Cushitic family of the Afro-Asiatic phylum. And also kebena have a lot of unique cultural celebrations such as Wedding, Mourning and Holydays Ceremony including traditional Proverbs and Thoughts.

There are a number of unique cultural materials that kebena people used in ancient era like that of feeding and dressing materials. Those cultural materials would have a very important role for researchers (historians).

                                      

We have 280 guests and no members online