የጋብቻ ሥርዓት በቀቤና

የጋብቻ  የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወጣቶች ለጋብቻ ብቁ መሆናቸው የሚገልፁባቸው የተለያዩ መንገዶች አሉዋቸው፡፡ ለምሣሌ አንዲት ልጃገረድ ለአቅመ ሔዋን መድረሷን ለማመልከትናኦታወይምጨረርየተሰኘውን ባህላዊ የፀጉር አሰራር ትሠራለች፡፡ የግል ቤትና ንብረት እንዲኖረው መፈለግና ይህም እንዲሟላለት ለወላጆቹ ጥያቄ ማቅረብ ደግሞ ወንዱ ለአቅመ አዳም መድረሱን የሚገለፅበት መንገድ ነው፡፡ በቀቤና ብሔረሰብ ሰባት የጋብቻ ዓይነቶች አሉ; እነሱም፡- “አጩቁ”- የሚባለውና በወላጆች መልካም ፈቃድ የሚፈፀም ጋብቻ፣ጌሡ”- በጠለፋ ወይም በኃይል የሚፈፀም ጋብቻ፣ጣጦቄን አዩ”- ድንገቴ የጋብቻ ዓይነት ሲሆን ጋብቻ፣ረጋኡ” - የውርስ ጋብቻ፣ዶርቱታ”- የምትክ ጋብቻ፣ወጌቲታ”- የፈት ጋብቻ፣ሙሪታ ባዬን አሱ”- የሴቷ ወላጆች ለልጆቻቸው የመረጡላትን ወንድ ጠርተው የሚድሩለት ጋብቻናቸው፡፡

ይሁን እንጂ በብሔረሰቡ ዘንድ በይበልጥ የሚዘወተሩት  “አጩቁአናጣጦቄን አዩንየተሰኙት የጋብቻ ዓይነቶች ብቻ ናቸው፡፡ አጩቁጋብቻ በወላጆች መልካም ፍቃድ የሚፈፀም የጋብቻ ዓይነት ሲሆን በዚህ የጋብቻ ሂደት ውስጥ ከፍተኛውን ሚና የሚጫወተው የወንዱ ወላጅ አባት አንደሆነ ይነገራል፡፡ አባት ለልጁ የወደፊት ሚስት ትሆንለት ዘንድ ወደመረጣት ልጃገረድ ቤተሰብ አብረውት የሚሄዱትን ሽማግሌዎችን የሚመርጠው እሱ ነው፡፡ ከመረጣቸው ሽማግሌዎች ጋር በመሆን ከልጅቷ ወላጅ አባት ቤት እንደደረሱምልጅህን ለልጄ ስጠኝየሚል የጋብቻ ጥያቄ የልጁ አባት ያቀርባል፡፡

  

በብሔረሰቡ የቆየ ልማድ መሠረት ለዚህ ዓይነቱ የጋብቻ ጥያቄአልሰጥም!” የሚል ቀጥተኛ ምላሽ ወዲያው መስጠትም ሆነ በማናቸውም መንገድ ጥያቄውን ይዘው የመጡትን ሽማግሌዎች አሳፍሮ መመለስ እንደፀያፍ ተግባር ይቆጠራል፡፡ ይህም ማለት ግን ለጥያቄው ሁሌም አዎንታዊ ምላሽ ይሰጣል; የጠየቀ ሁሉ ያገባል ማለት አይደለም፡፡ በቀጥታ አይሁን እንጂ ለሽማግሌዎች አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ምላሽ በተዘዋዋሪ የሚሰጥባቸውና በብሔረሰቡ የተለመዱ በርካታ መንገዶች አሉ; አጭር ወይም ረዥም ቀጠሮ መስጠት ዋነኛው ስልት ነው፡፡ የልጅቷ አባት በጉዳዩ ላይ ተማክሮ መልስ ለመስጠት ለሽማግሌዎቹ አጭር /ከሁለት ሣምንት ያልበለጠ/ ቀጠሮ ከሰጠ ጋብቻውን የፈቀደ ወይም በጋብቻው የተስማማ መሆኑን፣ ረዥም እስከ ሦስት ወር የሚቆይ ቀጠሮ ከሰጠ ደግሞ ጋብቻውን ያልፈቀደ  መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከሁለት ሣምንት ያልበለጠ ቀጠሮ የሚሰጣቸው ሽማግሌዎችም በቀጣዩ ቀጠሮ ሌሎች ሽማግሌዎችን ጨምረው ጫትና  ስኳር ይዘው  ወደ ልጅቷ ወላጅ አባት ቤት ይመለሳሉ፡፡  እንደተጠበቀውም  ከልጅቷ ወላጆች ልጃችንን አላህ ከሰጣችሁ እኛም ለልጃችሁ ሰጥተናልበማለት መስማማታቸውን ይገልፃሉ፡፡ ይህ የይሁንታ ምላሽ አንደተሰማም ኮርማ በሬ ታርዶ ይበላል፣  ኒካ” /ቀለበት/ ሥርዓትም ይፈፀማል፡፡ አንዲት የቀቤና ልጃገረድኒካከታሠረላት በኋላ ሌላ ማንም ወንድ አይደፍራትም፣ ትከበራለች፣ ትታፈራለችም፡፡ በሆነ አጋጣሚ በሌላ ወንድ ብትጠለፍ ወይም ብትደፈር ጠላፊው በቦኔህግ መሠረት ይቀጣል፡፡ ለድርጊቱምአቂድ” /ካሣ/ በብሔረሰቡ መንፈሳዊ መሪዎች አማካይነት ሁለቱም ወገኖች በቃላቸው ለመፅናትሰጥቻለሁ” “ተቀብያለሁበማለት ቃል ኪዳን  የሚገቡበት የቃል ኪዳን ሥርዓት ነው፡፡ ጠላፊው ወይም ደፋሪው ካሳ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡ የካሣው መጠንም በአማካይ 15ዐዐ-2ዐዐዐ ብር እንደሚደርስ ይገመታል፡፡

    ሌላው በብሔረሰቡ የሚዘወተረው የጋብቻ ዓይነትጣጦቄን አዩየሚሰኘው የድንገቴ ጋብቻ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ጋብቻ አንዳንዴተጠምጥሞ ገባበሚል ስያሜውም ይታወቃል፡፡ አግቢው ወጣት ከጓደኞቹ ጋር በመሆን ሣይታሰብ በድንገት ከወደዳት ልጅ ወላጆች ቤት ገብቶአልወጣምበማለቱ ምክንያት የሚፈፀም ጋብቻ በመሆኑ ነውተጠምጥሞ ገባመባሉ፡፡ ይህ ዓይነቱ ጋብቻ ለልጅቱ ወላጆች ዱብዕዳ /ድንገተኛ/ ይሁን አንጂ ለተጋቢዎች ግን ድንገተኛ አይደለም፡፡ በሁለቱ ተጋቢዎች መካከል ቀደም ሲል በሚስጢር የተስማሙበት ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ ዓይነት ከነጓደኞቹ የገባው ወጣት ከየት አንደመጣ? ምን እንደሚፈልግ? ቤታቸውንም ለቆ እንዲወጣ በልጅቷ ወላጆች ቢጠየቅም አይወጣም; ቤታቸውን የሙጥኝ ይላል፡፡ ከልጅቱ ወላጆች የይሁንታን ምላሽ እስከሚያገኝ ድረስ ከገባበት ቤት ንቅንቅ አይልም፡፡ ልጅቷም ፍቅረኛዋተጠምጥሞ መግባቱንስታውቅ ወዲያው በቅርብ ጓደኞቹ ትታጀባለች፣ አፍታም ሣይቆዩ የልጁ ወላጆች ልጃቸው ካለበት ከልጅቷ ወላጆች ቤት ሽማግሌ ይልካሉ፡፡ በዚህ መልኩ ጉዳዩ በሽምግልና ያልቅና ልጅቷ ትሞሸራለች፡፡ በተሞሸረች በአንድ ሁለት ቀን ውስጥም ጋብቻው ይፈፀማል፡፡ የጥሎሽ ሥርዓትም በዚሁ ዕለት ይከናወናል፡፡ የሚሰጠው የጥሎሽ ዓይነትና መጠን እንደሰጪው የመስጠት አቅም ይወሰናል፡፡ ከብት፣ ብር እና የተለያዩ አልባሳት ይሰጣሉ፡፡ ሆኖም ግን ይህ የጥሎሽ መጠን መናር በርካታ ወጣቶች ከጋብቻ እንዲርቁና እንዲሸሹ  በማድረጉ ምክንያት የጥሎሹ መጠን ወደ 15 ብር ዝቅ አንዲል በባህላዊ የአስተዳደር ጉባኤ ተወስኗል፡፡

ነፍሰ-ጡር የሆነች የቀቤና ሴት ልትወልድ አንድ ወይም ሁለት ወር ሲቀራት አይብ እንዲሁም ክትፎ /ከጐመንና ከስጋ/ አዘጋጅታ ጐረቤቶቿንና የቅርብ ዘመዶቿን ትጋብዛቸዋለች፡፡ ተጋባዦችም በአፀፋው በሠላም አንድትገላገል ይፀልዩላታል፡፡ ይህ ዓይነቱ ሥርዓትምጀበፍቲሡይባላል፡፡ እንዲሁም  አሁን ቀረ እንጂ ጥንት አንዲት አራስ ሴት ከአራስ ቤት እስከምትወጣ ድረስ ወላጅ እናቷ ክትፎ አዘጋጅታ ከቤቷ ድረስ የምታመጣላትመገንቤሱታየሚባል ባህላዊ ሥርዓት ሁሉ እንደነበረ የአካባቢው አዛውንቶች ያስታውሳሉ፡፡      

 

Download/Watch Kebena Wedding Cermony

 

We have 189 guests and no members online